Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በጽንፈኛው ህወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ የካፋ ዞን ነዋሪዎች ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አረመኔው የጁንታው ሕወሓት ቡድን የፈጸመውን ክህደት የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ነዋሪዎቹ እያካሄዱት ባለው ሰልፍ አረመኔው የጥፋት ቡድን ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ጠላት መሆኑን በመግለጽ የጥፋት ድርጊቱን እንዲሁም የጥፋት ቡድኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል።
ሰልፈኞቹ “መንግሥት ወንጀለኞቹን የሕወሓት ቡድን አባላት ለሕግ ለማቅረብ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን” ማለታቸውን ከካፋ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ነዋሪዎቹ ” ጁንታውን ቡድን እየተዋጋን፣ ልማታችንን እናስቀጥላለን ፣ከጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም የበኩላችንን እንወጣለን፣ በከሀዲው የሕወሓት ቡድን ሴራ አንድነታችን አይናጋም፣ አንድነታችንን አጠናክረን የሕወሓት እና የተላላኪዎቹን አፍራሽ ተልእኮን እናጋልጣለን፣ አጥፊው የሕወሓት ቡድን የፈጸመውን የሀገር ክህደት እኩይ ተግባር እናወግዛለን የሚሉ መፈክሮችንም አሰምተዋል::
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.