Fana: At a Speed of Life!

መንግስት እየወሰደ ባለው የህልውና ዘመቻ እና ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የኦሮሞ ዳያስፖራ አባላት ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት እየወሰደ ባለው የህልውና ዘመቻ እና ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የኦሮሞ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ውይይት ተካሂዷል።
የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያዘጋጀው ውይይት የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ሌንጮ ባቲ በተገኙበት ነው የተካሄደው።
በውይይቱ ላይ አትሌቶች እና አርቲስቶችን ጨምሮ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው የኦሮሞ ዳያስፖራዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
የኦሮሞ ዳያስፖራ የሀገር ውስጥ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲሁም ወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ የውይይቱ ዋነኛ አጀንዳዎች ናቸው።
በመድረኩ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.