Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የአሜሪካ ኤምባሲን አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ኤምባሲና ድርጅቶች የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨት መቀጠላቸውን ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ጠቅሰዋል።

‘ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ተከባለች’ የሚል መረጃን ያሰራጩ እንደነበር አውስተው ÷ አሁን ደግሞ ‘ሽብር ይፈፀማል’ የሚል ሀሰት መቀጠሉን ጠቁመዋል።

ኤምባሲውና የአሜሪካ መንግስት የሀሰት መረጃዎችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠቡም አስጠንቅቀዋል።

ኤምባሲው ከራሱ አልፎ ሌሎች ኤምባሲዎችንና ተቋማትን እንዲወጡ ጫና እያሳደረ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

ድርጊቱ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የሚጎዳ መሆኑን አንስተዋል።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሴራቸው እንዳይተባበሩ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።

‘የአሜሪካ እርዳታ ድርጅቶች እርዳታ ትተን እንወጣለን’ የሚል ማስፈራሪያ ማንሳታቸው ይሰማል ያሉት አቶ ከበደ ÷ ኢትዮጵያውያን ክብራችን በስንዴ አንለውጥም ብለዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.