Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የአርብቶአደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አርብቶአደሩ በሀገሪቱ ብሔራዊ ገቢ፣ ስራ አጥነትን ቅነሳ እና በግብርና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ።

ብሔራዊ የግመል ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ውይይት በሶማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ ተካሂዷል።

ውይይቱን የክልሉ የአርብቶአደር ጥናትና እርሻ ምርምር ተቋም ከጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት ያዘጋጁት ሲሆን የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን አርብቶ አደሩ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የራሱን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው መንግስት በአርብቶ አደሩ ዘንድ በተለይም የግመልን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና የኑሮ ትስስር ለማሳያነት በቅርቡ በታተመው የብር ኖትላይ የግመልን ምስል ማስቀመጡ አይዘነጋም ብለዋል።

በቀጣይነትም የግመልን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ለሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮቻች ጋር በመሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን የሰላም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.