Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት ከጎኑ እንቆማለን

አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ መንግስት ለሀገር ሰላምና የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ከጎኑ በመቆም የድርሻቸውን እንደሚወጡ በአፋር ክልል የሠመራ-ሎግያ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
መንግስት በተለይ ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራት ሰላም ያረጋግጣል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ነዋሪዎቹ ለኢዜአ ገልጸዋል።
አቶ አህመድ አብደላ በሰጡት አስተያየት፥ በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ የህዝብ ይሁንታ ያገኘው ፓርቲ መንግስት መመስረቱ የለውጡን ተስፋዎች የበለጠ ለማጎልበት አስተዋጽኦው የጎላ ነው ያሉት።
አዲሱ መንግስት የህብረተሰቡን ችግሮች በትኩረት የሚፈቱ፣ በሃላፊነት የሚሰሩና የተሻለ የትምህርት ዝግጅትና ቁርጠኝነት ያላቸው ሰዎችን ወደአመራርነት ያመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በተለይም ሀገርን ለማፍረስ በአሸባሪው ህውሃት የተጠነሰሰው ሴራ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማክሸፍ የህዝብ ሰላምን ማረጋገጥ ቀዳሚ ሥራው ሊያደርግ እንደሚገባ አመልክተዋል።
መንግስት የሀገርና የህዝብ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያከናውነው ሥራ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመው ፥ እሳቸውም የከተማቸውን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
ወጣት ተካልኝ መስቀል በበኩሉ ፤ በዴሞክራሲያዊ ሂደት በተመሰረተው አዲሱ መንግስት ላይ ህዝቡ ብዙ ተስፋ መጣሉን ገልጿል።
ለወጣቶች የተሻለ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለማርገብ አዲሱ መንግስት ትኩረት ይሰጣል ብሎ እንደሚጠብቅ ተናግረዋል።
የውስጥ እና የውጭ ጸረ-ሠላም ሃይሎች በቅንጅት የጀመሩትን ሀገር የማፍረስ ሴራ ማክሸፍ የመንግስት ቀዳሚ ተግባሩ እንደሚሆን ተስፋ አደጋለሁ ብሏል።
የህብረተሰቡ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝና ህገወጥነትን ለመዋጋት ከመንግስት ጎን በመቆም የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም ወጣት ተካልኝ አስታውቀዋል።
የመንግስት ምስረታ ሂደቱ በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ፍላጎታቸውን መጫን ለሚፈልጉ አካላት ትምህርት የሚሰጥ ነው” ያሉት ደግሞ አቶ ኡመር ኢብሒሂም ናቸው።
“የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ላልወጡ ሃይሎችና ተላላኪዎቻቸው ፍላጎት ፈጽሞ እንደማይሳካ የራሱን መንግስት በመመስረት አሳይቷል” ብለዋል።
በብዙ ጫና እና ችግር ውስጥ ሆና የተመሠረተው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ብዙ ሥራዎች ቢጠብቁትም ቅድሚያ ቁልፍ ተግባር የህብረተሰብ ጥያቄዎችን መመለስ እንዳለበት ነው ያመለከቱት።
እንደ አስተያየት ሰጪው መንግስት ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ብለው የተነሱ ሽፍታዎችና ጋሻጃግሬዎቻውን በማያዳግም ሁኔታ አደብ ማስገዛት የመጀመሪያው ተግባሩ መሆን ይኖርበታል።
እየተስተዋለ ያለውን የኢኮኖሚ አሻጥር ማስቆም ሌላው አዲሱ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ጉዳዮች መካከል የሚጠቀስ ነው ብለዋል።
” አዲሱ መንግስት ከምርጫው እስከ መንግስት ምስረታ ባለው ሂደት ከእስከዛሬ በተሻለ የህዝብው ውክልና ያለው መሆኑን በተግባር ታይቷል” ያሉት ደግሞ አቶ ከቢር ሁመድ ናቸው።
በቀጣይ በሀገሪቱ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲን በማረጋገጥ ተጨባጭ ለውጦችን በማስመዝገብ ብቃቱን ይበልጥ በስራ ያረጋግጣል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
ህዝብን ላልተገባ የዋጋ ንረት እየዳረገ ያለውን ሙስናና ብልሹ አስተዳደር በፍጥነት ማረም ከአዲሱ መንግስት እንደሚጠብቁና ለእዚህም የበኩላቸውን ለመወጣት እንደሚጥሩ ተናግረዋል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.