Fana: At a Speed of Life!

መካነሰላም እና ከላላ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መካነሰላም እና ከላላ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ቡድን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የወደመባቸው ከተሞች የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮችንና ምሰሶዎችን በመጠገን የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደሴ ዲስትሪክት ስር የሚገኙትን ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ከሚሴ፣ ባቲ፣ ማጀቴ፣ ጨፋ ሮቢት፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት፣ ሳይንት አጅባር፣ መኮይና አልብኮ ከተሞችን እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ኤሌክትሪክ የሰጠ ሲሆን: አሁንም ሌሎች ቀሪ ከተሞችን ለማገኛኘት ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል ነው የተባለው፡፡

በዚህም መሰረት የከተሞቻችንን ኤሌክትሪክ መልሰን ሳናገናኝ እረፍት የሚባል ነገር የለም በማለት ቆርጠው የተነሱት የደሴ ዲስትሪክት ሰራተኞች ዛሬ እሁድ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም የመካነ ሰላም እና ከላላ ከተሞች የሚሰጠውን የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና በማጠናቀቅ ከተሞቹ ወራሪው ቡድን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.