Fana: At a Speed of Life!

መውሊድ ሲከበር የነቢዩ መሐመድን በረከቶች በማስተዋልና መንገዳቸውን በማሰብ መሆን አለበት – ሃጂ ዑመር እድሪስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 496ኛው መውሊድ ሲከበር የነቢዩ መሐመድን በረከቶች በማስተዋልና መንገዳቸውን በማሰብ መሆን እንዳለበት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ አሳስበዋል።
1ሺህ 496ኛው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል ነገ በመላ ኢትዮጵያ ተከብሮ ይውላል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በዓሉን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ባስተላለፉት በዚሁ ምልዕክታቸው፥ ነቢዩ መሐመድ የተወለዱት መልካም ነገሮችን ሊያስተምሩ፥ መጥፎ ነገሮችን ሊቃወሙ በመሆኑ መልካም ስራቸውን በማየት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ መውሊድ እንደሚከበር አስረድተዋል።
በዓሉ ሲከበር የነቢዩ መሐመድን በረከቶች በማስተዋልና መንገዳቸውን በማሰብ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አቅም የሌላቸውን በመጎብኘትና ካለው በማካፈል እንዲሆንም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ጥሪ አቅርበዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ፥ በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ገንዘብ በማሰባሰብ በሠላም ሚኒስቴር በኩል በተዘጋጀ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉንም ገልጸዋል።
መንግስት በተለያየ ችግር ላይ ያሉ ዜጎችን መደገፍና የሚሰጠው ድጋፉም ለተጎዱ ወገኖች መድረሱን ሊያረጋግጥ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የመውሊድ በዓል የሠላም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል።
“አገራችንን አላህ አማን ያድርግልን፣ የአውሬን ጠባይ ከሰው ጠባይ ላይ አላህ ያንሳልን፤ የሚያፈያቃቅር ፣ የሚያቀራርብና የሚያመካክር ነገር አላህ ይስጠን” ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.