Fana: At a Speed of Life!

መደበኛ የግብርና ስራቸውን እየከወኑ መሆኑን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መደበኛ የግብርና ስራቸውን እየከወኑ እንደሚገኙ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪዎች እና በልማት የተሰማሩ ባለሃብቶ ተናገሩ።
ለበርካታ ዓመታት በአሸባሪው ትህነግ ግፍ እና በደል ሲደርስባቸው የነበሩ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት አንድም መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል መደበኛ የግብርና ስራቸውን እያከናወኑ እንደሚገኝ ከሰሞኑ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባልደረቦች በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።
ከፍተኛ የሰሊጥ የጥጥ እና የማሽላ ምርት ከሚገኝባቸው ምዕራባዊ ቆላማ ዞኖች አንዱ በመሆኑ በየአመቱ ከተለያዩ አካባቢዎች ለቀን ስራ በርካታ ወጣቶች ወደ ስፍራው ያመራሉ።
በጥቅምት ወር በአሸባሪው ትህነግ በማይካድራ በደረሰው ጭፍጨፋ በርካታ የቀን ሰራተኞች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ተከትሎ በዚህ አመት ከፀጥታ ስጋት ጋር ተያይዞ የሰራተኛ እጥረት እንዳያጋጥም ባለ ሃብቶቹ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አለልኝ በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ ከመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር በተሰራው ስራ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ዞኑ በመምጣት በተለያዩ የስራ መስኮች መሳተፍ እንደሚችል ተናግረዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.