Fana: At a Speed of Life!

መድሃኒትን ለተላመደ የቲቢ በሽታ ከ18 እስከ 24 ወራት ይሰጥ የነበረው ህክምና ከ9 እስከ 12 ወራት በሚሰጥ መድሐኒት ተተካ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መድሃኒትን ለተላመደ ለቲቢ በሽታ ከዚህ በፊት ከ18 እስከ 24 ወራት ይሰጥ የነበረው የህክምና አገልግሎት ከ9 እስከ 12 ወራት በሚሰጥ መድሐኒት መተካቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ህክምናው ከዚህ ቀደም በመርፌና በሚዋጥ መድሃኒት መልክ ሲሰጥ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን በሚዋጥ መድሃኒት መተካቱ ነው የተጠቀሰው፡፡

በዛሬው ዕለት መድሐኒቱን የተላመደ የቲቢ በሽታ ህክምና ለሚከታተሉ ታካሚዎች በአጭር ጊዜ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል የማስጀመሪያ ስነ- ስርዓት ተካሄዷል፡፡

በዚሁ ወቅት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ምክትል ዳይሬክተርና የብሔራዊ ቲቢ መከላከል ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ታዬ ለታ መድሃኒቱን የተላመደ የቲቢ በሽታ በማህበረሰቡ ዘንድ እየፈጠረ ያለው ተጽዕኖ ከባድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የበሽታውን አሳሳቢነት በመመልከትና ትኩረት በመስጠት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ በመከላከልና በበሽታው ለተያዙ ህሙማን ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ዙሪያ ጥናት እንዲደረግ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ኢትዮጵያም የጥናቱ ተሳታፊ በመሆን ውጤታማ የሆነ ጥናት ማካሄዷን ነው ያነሱት፡፡

አዲሱ የሚዋጠው መድሐኒት ለህሙማኑ ከፍተኛ ጫና የሚቀንስና እፎይታን እንደሚሰጥ በመግለጽ ህክምናውን ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እንደተጠናቀቀም አስታውቀዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው አካላትም የህክምና አገልግሎቱ የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ አቶ ታዬ ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.