Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያና ግብፅን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት  ለማጠናከር የሚያግዙ  መስራት ይጠበቅባቸዋል- አምባሳደር ማርቆስ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በግብፅ ባለሙሉ ስልጣን  አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ካይሮ ለሚገኙ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብንና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ  ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይም ኢትዮጵያ እና ግብጽ በሃይማኖት  እና በተፈጥሮ የተጋመዱ ሀገሮች መሆናቸዉን  ገልፀዋል።

መገናኛ ብዙሃንም የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት  ለማጠናከር የሚያግዙ አዎንታዊ ዘገባዎችን የማውጣት  ኃላፊነት እንዳለባቸው አምባሳደሩ ገልፀዋል።

አምባሳደር ማርቆስ  በትግራይ ክልል ስለካሄደው  የህግ ማስከበር እርምጃ፣ በክልሉ ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ስለተደረገዉ ጥረት፣ ሰብአዊ እርዳታ ለተረጂዎች እንዲደርስ እየተደረገ ስላለዉ ጥረት፣ ጉዳት የደረሳበቸው መሰረተ ልማቶች መልሶ የመገንባት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ስለተጀመረው የምርመራ ሂደትን በተመለከተ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የህዳሴዉ ግድብ ግንባታ እና ድርድር ሂደትን በተመለከተም  ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት ለሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ከፍተኛ እምነት እንዳላት ገልጸው፤  ልዩነቶች በድርድር እንዲፈቱ ጥረት እንደምታደርግም ነው የተናገሩት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.