Fana: At a Speed of Life!

መፈንቅለ መንግስቱን የመሩት ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ የማሊ የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሊ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ወታደራዊ መሪውን ኮሎኔል አሲሚ ጎይታን የሃገሪቱ የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሰየመ፡፡

ኮሎኔል ጎይታ ከቀናት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን ከያዙ በኋላ የሃገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ ማወጃቸው ይታወሳል፡፡

ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ሃገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር እንዲመልስ የተመረጠው አስተዳደር ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ባህ ንዳው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞክታር ኦኔ በቁጥጥር ስር ውለው ከቀናት በኋላ ተለቀዋል፡፡

ኮሎኔል ጎይታም ሁለቱ ባለስልጣናት ሃላፊነታቸውን ያልተወጡና የሽግግር ጊዜ ላይ አሲረዋል በሚል ወንጅለዋቸዋል፡፡

ኮሎኔል ጎይታ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለተኛውን መፈንቅለ መንግሥት ያደረጉ ሲሆን፥ በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡትን ፕሬዚዳንት ቡባካር ኬይታን ባለፈው ነሐሴ ወር ከመንበራቸው ማስወገዳቸው ይታወሳል፡፡

ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ የሽግግር መንግስቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፥ ባለፈው ዓመት የመሩትን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የ18 ወራት የሽግግር ምክር ቤት ተሰይሞ ነበር።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.