Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በኤሮስፔስና ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጅ ዙሪያ ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጋር እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኤሮስፔስና ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጅ ዘርፎች ዙሪያ ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት ሚኒስቴሩ በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጅ እና ኤሮስፔስ ላይ ለመስራት ከተሰማራው ፋሪስ ከተሰኘ ኢንስቲቲዩት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና የፋሪስ ቴክኖሎጅ ኢንስቲቲዩት መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ ይርዳው ተፈራርመውታል።

ስምምነቱ ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጅ፣ ኤሮስፔስና ሌሎች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለጸው።

ፋሪስ በወጣት ኢትዮጵያውያን ኢንጅነሮች እና የፈጠራ ባለሙያዎች የተቋቋመ ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጅ፣ ኤሮስፔስና መሰል ዘርፎች ላይ የሚሰራ ኢንስቲቲዩት መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.