Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ከተሞች የኮሮና ወረርሽኝን ወደ መከላከል ስራ ፊታቸውን ማዞር እንዳለባቸው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 22፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ከተሞች የመዋዕለ ንዋይ ዕቅዳቸውን ከልሰው ወረርሽኙን ወደ መከላከል ስራ ፊታቸውን በማዞር መስራት እንዳለባቸው ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ÷መንግስት ኮቮድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ የሚገኝ በመሆኑ ይህንኑ ተልዕኮ በመጋራት በውጤታማነት ለመከላከል እንዲቻል ከተሞች የሚጠበቅባቸውን ድረሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስቧል።

በከተማ ልማትና ኮንንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ማሻሻያ፣ ፈንድ ሞቢላይዜሽንና ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አምላኩ አዳሙ ÷ የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ በሚገኙ 117 ከተሞች እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዓመትም ከ3 ሺህ 610 ያለነሱ ፕሮጀክቶችን በእቅድ ይዘው እየተተገበሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት በአለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከተሞች ለአቅም ግንባታ ሥራ የተያዘላቸውን በጀት ወረርሽኙን ወደ መከላከል ስራ በማዞር መስራት አለባቸው ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ ከተሞች የወረርሽኙን አስከፊነት በመገንዘብ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም የማይጠቀሙበት በጀት ካላቸውም ቅድሚያ ወረርሽኙን ለመከላከል ትኩረት ሰጥተው መስራት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት ፡፡

ሃላፊው አያይዘውም በእነዚህ 117 ከተሞች እየሰሩ የሚገኙትን የፕሮጀክት ሰራተኞችና በፕሮጀክቱ በተለያዩ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙትን  በርካታ የሰው ኃይል ለመታደግ ሁሉም ከተሞች ትኩረት አድረገው መስራት አለባቸው  ማለታቸውን ከከተማ ልማትና ኮንንስትራክሽን ሚኒስቴር  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.