Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ከአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች ጋር መከረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች ጋር አገር አቀፍ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚልን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፥ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሚሰሯቸው ዋና ዋና ስራዎች ላይና መተግበር ያለባቸው አዳዲስ አሰራሮች ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል÷ “ያለፈ ታሪክ ዘካሪ ብቻ ሆነን መቅረት የለብንም የራሳችንን ታሪክ ሰርተን ለቀጣዩ ትውልድ የማሻገር ሀላፊነት አለብን” ብለዋል::
በኢኮኖሚ ዘርፍ ራሷን ችላ የምትቆም ነፃ የሆነች ሀገር እንድትሆን መስራት ይኖርብናልም ነው ያሉት፡፡
ቀጥሎ ለሚጠበቅ ምዕራፍ የተለየ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ የወጣቶችን እምቅ አቅም መጠቀም እና የስራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ ባህል እንዲኖር መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ይህንን የሚያግዝ ስራ ፈጠራዎች በቴክኖሎጂ የሚደገፉበት ስርዓትን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም መዘርጋቱን ነው ያመለከቱት።
በዘቢብ ተክላይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.