Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ከዩኒሴፍ ጋር የውሃ ችግር በተከሰተባቸው አከባቢዎች ውሃ ለማቅረብ ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ዩኒሴፍ በጦርነትና በድርቅ ምክንያት የውሃ እጦት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ውሃ ለማቅረብ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
 
በተለይም በጦርነት የወደሙ የውሃ መሰረተ ልቶችን በመጠገን ችግሮቹን በዘላቂነት መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡
 
የውሃና ኢርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጀነር ሃብታሙ ኢተፋ እና በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ጊዜያዊ ተወካይ ጂያንፍራንኮ ሮቲግሊያኖ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡
 
በአፋርና አማራ ክልሎች በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ የውሃ እና የኢነርጂ መሰረተ ልማቶችን በመለየት አስፈላጊውን ጥገና የማድረግ ስራ መጀመሩን ሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡
 
ወራሪው በገባባቸው አካባቢዎች ያደረሳቸው ውድመቶች የዜጎችን ኑሮ ያቃወሰ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡
 
ድርቅ እያጠቃቸው ባሉ ሶማሌ ፣ አፋርና ከፊል የኦሮሚያ ክልሎችም ያለውን ችግር ለመፍታት በውሃ እና በሃይል አቅርቦት ላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
 
በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ጊዜያዊ ተወካይ በበኩላቸው በጦርነቱ ያደረሰው ጉዳት አፋጣኝ መፍትሄ የሚያሻው መሆኑን በመግለጽ በተለይ መሰረታዊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት በመጠገን ዜጎችን ወደቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ ከመንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በድርቅ የተጎዱ አከባቢዎችን ለመደገፍም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመቀናጀት የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.