Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምርታማነትን የሚያረጋግጡ 37 ትራክተሮችን ለክልሎች አከፋፈለ 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ 37 ትራክተሮችን ለተለያዩ ክልሎች አከፋፍሏል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ነው ድጋፉን ያደረገው።

ድጋፋ በዋናነት በግብርናው ዘርፍ ስልጠና ወስደውና ገንዘብ ቆጥበው ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት ላይ ለነበሩ ወጣቶች የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ወጣቶች ወደስራ እንዲገቡ የሚያሥችላቸውን ድጋፍ አድርገናል ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ወጣቱ ለእኩይ አላማ መጠቀሚያ እንዳይሆን እራሱን በሚያሳድጉ ስራዎችን ጊዜውን ማሳለፍ ይገባዋልም ብለዋል።

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስኪያጅ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው የውጭ ምንዛሬን ለማስቀረት እና ግብርናውን ለማዘመን ድጋፉ ድርሻው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

 

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.