Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ በትግራይ ክልል ለተጎዱ ዜጎች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ ክልል በግጭት ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ማኅበሩ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው 2 ሺህ ዜጎች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ልዩ ልዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ብርድ ልብስ፣ ምንጣፍ፣ የመመገቢያ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና መሠረታዊ መድኃኒት ማህበሩ ካደረጋቸው ድጋፎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ማህበሩ ከዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ፣ የአምቡላንስ አገልግሎት፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን የማገናኘት፣ የተለያዩ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፎችን አድርጓል፡፡

ማኅበሩ በመቐለ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሀ እጥረት ተከትሎ ለከተማዋ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሀ ድጋፍ ማድረጉን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.