Fana: At a Speed of Life!

ማላዊ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ማላዊ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለፀች፡፡
በኬንያ የማላዊ አምባሳደር አግሪና ሙሳ በኬንያ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለምን ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ወቅት አምባሳደሯ ማላዊ ከኢትዮጵያጋር በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በንግድ እና በአቪዬሽን መስኮች ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
በተጨማሪም ሃገራቸው በውጭ ግንኙነት አገልግሎት ስልጠና ዙሪያ ከኢትዮጵያ ልምድ የመቅሰም ፍላጎት እንዳላት አምባሳደሯ ተናግረዋል።
አምባሳደር ሙሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማላዊ አየር መንገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልፀው፣ አየር መንገዱ ሃገራቸውን ከሌሎች ሃገራት ጋር በማገናኘት ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
አምባሳደር መለስ በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመሩ የትብብር መስኮችን ማንቀሳቀስ እንደሚገባ መግለፃቸውን በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.