Fana: At a Speed of Life!

ማራቶን ሞተርስ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠም ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ማራቶን ሞተርስ ኢንጂነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በመጭዎቹ 3 ወራት መገጣጠም ሊጀምር ነው።

ኩባንያው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሃዩንዳይ ምርቶችን በመጭዎቹ ሶስት ወራት ለመገጣጠም የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም መኪናዎችን ለመገጣጠም የሚያስችሉ እቃዎችን ከውጭ የማስገባቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

ተሽከርካሪዎቹ በቀላሉ ቤት ውስጥ በሚገኝ ኤሌክትሪክ ሊሞሉ የሚችሉ ከመሆናቸው በላይ የመኪና ዘይቶችን እና ቅባቶችን የማይጠቀሙ መሆኑም ተመላክቷል።

ይህም ሀገሪቱ መሰል ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀር መሆኑ ነው የተገለጸው።

ተሽከርካሪዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ይቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥5 በመቶ የኤክሳይስ ታክስ ይጣልባቸዋል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.