Fana: At a Speed of Life!

ማንበብ እና መፃፍ የማይችሉት የፌስቱላ የቀዶ ህክምና ባለሙያ ኢትዮጵያዊቷ ማሚቱ ጋሼ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዴሊይ ሜል ማንበብ እና መፃፍ ሳይችሉ ትልቅ የቀዶ ህክምና ባለሙያ የሆኑትን ኢትዮጵያዊት እናት አስተዋውቋል።
ወይዘሮ ማሚቱ ጋሼ የተባሉት እናት በእርግዝና ላይ በነበሩበት ወቅት ህፃኑ በሆዳቸው ውስጥ እያለ ህይወቱ በማለፉ ለፌስቱላ ህመም ተጋልጠዋል ።
ይህ የህይወት አጋጣሚም ለህክምና በፈረንጆቹ 1963 በኢትዮጵያ የፌስቱላ ህክምና ወደ ሚሰጡት ዶክተር ካትሪን ሃምሊን ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ እድርጓቸዋል።
በዚህም በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው ዶክተር ካትሪን ሃምሊን የህይወት ዘመን ጓደኛ እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል።
አሁን ላይ የ73 ዓመት አዛውንት የሆኑት ወይዘሮ ማሚቱ ጋሼ ከዶክተር ካትሪን ሃምሊን ጋር ከመሰረቱት የህይወት ዘመን ጓደኝነት ጋር ተያይዞ ውስብስቡን የፌስቱላ ህክምና ሂደት እንዲማሩ እንዳስቻላቸው ነው ዘገባው ያስነበባው።
ከፌስቱላ ህመም ህይወታቸው የተፈረፈው ማንበብና መፃፉ የማይችሉት አዛውንቷ ከዶክተር ካትሪን ሃሚሊን ህልፈተ ህይወት በኋላ ለፌስትሉ ህሙማን የቀዶ
ህክምና በመስጠት ውርሳቸውን እያስቀጠሉ ይገኛሉ ተብሏል።
ወይዘሮ ማሚቱ ጋሼን የሚዘክረውን ሙሉ ዘገባ ከዴይሊ ሜል ድረ ገፅ https://www.dailymail.co.uk/…/Ethiopian-Mamitu-Gashe… ማግኘት ይቻላል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.