Fana: At a Speed of Life!

ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳይፈፀሙ መስራት እንደሚያስፈልግ የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳይፈፀሙ መስራት ያሻል አለ የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፡፡

ጉባኤው ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሁለት ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ማንነትን መሰረት አድርጎ ለተፈፀመው ጥቃት መንግስት መሰረታዊ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።

በመግለጫውም በተለያዩ አካባቢዎች አነስተኛ ቁጥር ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መንግስት ልዩ ጥበቃ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ማንነትን መሰረት በማድረግ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለማስቀረት መዋቅራዊ በሆነ መልኩ መፍታት ያስፈልጋል፤ ለዚህም የህገመንግስት ማሻሻያ ያሻል ብሏል በመግለጫው፡፡

የፌዴራል መንግስትም ችግሩን ከስሩ ለመፍታት የማያዳግም አርምጃ እንዲወስድ በመግለጫው ጠይቋል።

መዋቅራዊ ችግሩ በሰከነ ፖለቲካዊ መንገድ እንዲፈታ ሁሉም ወገን ከስሜታዊነት ወጥቶ በአብሮነት እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን ብሏል የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.