Fana: At a Speed of Life!

ማዕከላዊ ዕዙ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ለሚቃጣ ማናቸውም ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ዕዝ በሀገራችን ሉዓላዊነት ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ አሸባሪዎችን መደምሰስ በሚያስችል ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ማዕከላዊ ዕዝ “ስልጠና ለተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም” በሚል መርህ በተሠጠው የአመራር ሥልጠና በምንም የማይበገር አዋጊና ተዋጊ አባላትን ማፍራት እንደተቻለ የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ ተናግረዋል።

“በሳል አመራር ብቁ ተዋጊ የሠራዊት አባላትን ለማፍራት አይቸገርም” ያሉት ጀኔራል መኮንኑ የማዕከላዊ ዕዝ አመራሮች የሠራዊቱን ሞራላዊና ሥነ ልቦናዊ ዝግጁነት በመገንባት ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

“ዕዙ በአሁኑ ሰዓት የታጠቀው መሣሪያ ብቻ ሳይሆን የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ጭምር ነው” ያሉት ደግሞ በዕዙ የኮር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ ሲሆኑ በሥልጠና የተገኘውን የተሟላ ዝግጁነት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

የማዕከላዊ ዕዝ በተሰጠው የግዳጅ ቀጠና በሀገራችን ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ አሸባሪዎችን መደምሰስ በሚያስችለው አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ከመከላከያ ሠራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.