Fana: At a Speed of Life!

ማዕከላዊ ዕዝ የትኛውንም የጠላት ኃይል መደምሰስ የሚያስችል ወታደራዊ አቅም ገንብቷል- ሌ/ጀነራል ዘውዱ በላይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማዕከላዊ ዕዝ ሀገርን ሊያሸብር የሚያስብ ማናቸውንም የጠላት ኃይል መደምሰስ የሚያስችል ወታደራዊ አቅም መገንባቱን የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ ገለጹ፡፡

ማዕከላዊ ዕዝ በተለያየ የመሬት ገፅታ ላይ ሊያጋጥም የሚችል ጠላት ላይ ድል ለመቀዳጀት እና ለመደምሰስ የሚያስችለውን ወታደራዊ ልምምድ ማድረጉን ሌተናል ጀነራል ዘውዱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በተለያየ መንገድ ሃገር የማፍረስ አጀንዳ ይዘው በመንቀሳቀስ የህዝቡን ሰላም ለማወክ በሚዳክሩ የጥፋት ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውስድ እና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሰራዊታችን ወታደራዊ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ገንብቷል ነው ያሉት ሌተናል ጀነራሉ።

በዕዙ የኮር አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ረጋሳ በበኩላቸው፥ ሰራዊቱ ከዚህ ቀደም ከጠላት ጋር ባካሄዳቸው የአውደ ውጊያ ውሎዎች በርካታ ልምድና ተሞክሮዎች ማግኘቱን ጠቁመው÷ አሁን ላይ ያደርጋቸው ወታደራዊ ልምምዶች የዝግጁነት ደረጃውን ያሳደገበት ነው ብለዋል።

በዕዝ ደረጃ በተካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ላይ የተገኙ የዕዝ፣ የኮር እና የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች ሰራዊቱ የደረሰበትን ግዳጅ የመፈፀም አቅም ማድነቃቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ማዕከላዊ ዕዝ ለኢትዮጵያ ሰላም መጠበቅ እስከ ህይወት ዋጋ መክፈል የሚችሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ያሉበት እና ህብረት ያደመቀው የሰራዊት ክፍል መሆኑ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.