Fana: At a Speed of Life!

ማይክሮሶፍት አዲስ የደህንነት ስርዓት ለሊኑክስ ተጠቃሚዎች አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለሊኑክስ ተጠቃሚዎች አዲስ የደህንነት ማስጠበቂያ ስርዓት ማቅረቡን አስታወቀ፡፡
ማይክሮሶፍት ያቀረበው ሥርዓት ለሊኑክስ ተጠቃሚዎች የሚሆን ኢንድ ፖይንት ዲቴክሽን ሪስፖንስ የተባለ የደህንነት ማስጠበቂያ ነው ተብሏል፡፡
የበይነ መረብ ጥቃት መከላከያ ሥርዓቱ ስጋቶችን ለመቀነስ፣ ተከታታይ በሆነ መልኩ የኮምፒውተር ሲስተሞችን ለመቆጣጣር እና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል፡፡
በማይክሮሶፍት የቀረበው አዲሱ የኢንድፖይንት ዲቴክሽን ሪስፖንስ ስርዓት የመረጃ መንታፊዎች የሊኑክስ ሰርቨሮችን ኢላማ በማድረግ ሊፈጽሙ ያሰቡትን የጥቃት እንቅስቃሴ መለየት የሚያስችል ሲሆን በዚህም ለአድሚኖች እና ለበይነ መረብ ደህንነት ቡድን ድጋፍ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
ከዚህ ባሻገር ስርዓቱ አውቶማቲክ በሆነ መልኩ ለደህንነት መጠበቂያ አካላት የማንቂያ ድምጽ በማሰማት ጉዳቶችን ለመቀነስ እና ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ይህን ለመጠቀመም የሲስተም አድሚኖች በሊኑክስ የኢንተርፕራይዝ መገልገያቸው ላይ አንስብል ወይም ፑፔት እንዲሁም በማንኛውም ሌላ የሊኑክስ ውቅር አድሚኒስትሬቲቭ መሣሪያ እገዛ ሊተገብሩት እና ሊያዋቅሩት እንደሚችሉ ታውቋል፡፡
በመሆኑም ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም የማይክሮሶፍት ዲፌንደር ኢንድፖይንትን ለሊኑክስ እየተጠቀሙ ከሆነ አዲሱን ስሪት (version 101.18.53) ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን ያለምንም እንከን ማዘመን እንደሚችሉ ማይክሮሶፍት የምርት ሥራ አስኪያጅ ቶመር ሄቭሊን መግለጻቸውን ኢመደኤ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.