Fana: At a Speed of Life!

ማይክሮሶፍት የቲክቶክ የአሜሪካ ድርሻን ለመግዛት ድርድሩን ሊቀጥል ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክ መተግበሪያ ከአሜሪካ ሊታገድ ይችላል ማለታቸውን ተከትሎ ማይክሮሶፍት የቲክቶክ የአሜሪካ ድርሻን ለመግዛት ሲያደርገው የነበረውን ድርድር ማቋረጡ የሚታወስ ነው።

የማይክሮስፍት ሃላፊ ሳትያ ናዴላ ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ድርድሩ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

ኩባንያው ዶናልድ ትራምፕ ከሀገራዊ ደህንነት ጋር ተያይዞ ያቀረቡት ስጋት እንደሚረዳ አስታውቋል።

በመሆኑም ከደህነት ጋር ተያይዞ አስፈላጊው ማጣራት እንደሚካሄድ ነው ኩባንያው የገለፀው።

ማይክሮሶፍት የቲክቶክ የአሜሪካ ድርሻ ግዥ መፈፀም ያለውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታም ለአሜሪካ መንግስት እንደሚያቀርብ ነው ተነግሯል።

የተወሰኑ የአሜሪካ ፓለቲከኞች ቲክቶክ የአሜሪካ ዜጎችን የግል መረጃ አሳልፎ በመስጠት የደህንነት ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል።

ኩባንያው በበኩሉ የአሜሪካውያን መረጃዎች በአሜሪካ የመረጃ ቋት ብቻ የሚቀመጡ በመሆኑ ስጋት ሊኖር አይገባም በማለት የሚቀርብበትን ክስ አጥጥሏል።

ቲክቶክ በዓለም አቀፍ ደረጃ 500 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት የሚነገር ሲሆን 80 ሚሊየኖቹ ደግሞ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ደንበኞች መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

ቲክቶክ አጫጭር ቪዲዮን ማጋራት አገልግሎት የሚሰጥ ማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.