Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በሀረሪ ክልል በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተደርጓል – ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ነገ የሚካሄደው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ወደስራ መገባቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ነስሪ ዘከሪያ ገልጸዋል፡፡
የቅድመ ምርጫ፣ የምርጫው እለትና ድህረ ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንም ነው የተናገሩት፡፡
ምርጫው በሚካሄድባቸው 229 የምርጫ ጣቢያዎች የፀጥታ አካሉ በቋሚነት ጥበቃ እንደሚያደርግና እስካሁንም ለምርጫው እንቅፋት ይሆናሉ የተባሉ ችግሮች አለመኖራቸውን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።
ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት ድምፁን መስጠት እንደሚችል የጠቆሙት ኮሚሽነር ነስሪ÷ በተለይም ወጣቱ አካባቢውን በንቃት መጠበቅና አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን ሲያይ ለፀጥታ ኃይሉ እንዲጠቁም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በሀረሪ ክልል ሁለት የምርጫ ክልሎችና በከተማና ገጠር በሰላሳ ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ ነገ ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.