Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በትብብር እየሰራን ነው- የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን በጋምቤላ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ገለጹ።

የብልጽግና ፓርቲ ጋምቤላ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክድር ላክባክ እንዳሉት፤ ብልጽግና በክልሉ ከሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ካለፈው ዓመት ጀምሮ በትብብር እየሰራ ይገኛል።

መጭው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፍጹም ተአማኒነት ያለው ሆኖ ፍፃሜውን እንዲያገኝ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ / ጋህነን/ ጸሐፊ አቶ ተዘራ ኃለማሪያም ናቸው።

በቀጣይም ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲዎችም ሆኑ መላው የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባ አቶ ተዘራ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ምክትል መሪ ኮማንደር ጋድቤል ቦል በበኩላቸው ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ኢዜማ በክልል ከሚገኙ ሌሎች ፓርቲዎች ጋር እየሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.