Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ቦርድ አዲሱን አርማውን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዲሱን አርማውን ይፋ አደረገ።

የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

ቦርዱም አዲሱን አርማውን በዚህ ወቅት ይፋ አድርጓል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተቋሙ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ተአማኒ እንዲሆን በርካታ የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

የአሰራር ስርአቶችን በማሻሻል እና ተቋማዊ ለውጡ ቀጣዩን ምርጫ በስኬት ለማካሄድ አቅም የሚሰጥ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶታልም ነው ያሉት።

ቦርዱ ዘመናዊ የአሰራር ስርአቶችን እየዘረጋ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

የኮንፈረንሱ አላማም የለውጥ ሂደቱ ላይ ተጨማሪ ግብአቶች ለመሰብሰብና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለምርጫው ሰላማዊነት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ምክክር የሚደረግበት መሆኑንም ገልጸዋል።

በኮንፈረንሱ ያለፈው አንድ አመት የቦርዱን የለውጥ ሂደትና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር የሚደረግ ሲሆን የሲዳማ ዞን ህዝበ ውሳኔ ሂደት ተሞክሮዎችም ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም የ2012 የተከለሰ አጠቃላይ የምርጫ ሰሌዳ ይፋ ይደረጋል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

በሃይለእየሱስ መኮንን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.