Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ እና ህዝበ ውሳኔ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ውጤታቸውን ደምረው የጨረሱ የምርጫ ክልሎች ወደ ማዕከል አያመጡ ነው-ቦርዱ

አዲስ አበባ፣መስከረም፣25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርጫ እና ህዝበ ውሳኔ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ውጤታቸውን ደምረው የጨረሱ የምርጫ ክልሎች ወደ ማዕከል አያመጡ መሆኑን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡

ቦርዱ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በሃረሪ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ክልል በተካሄደው ምርጫ እና ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊዋ ሶሊያና ሽመልስ በተካሄደው ምርጫ እና ህዝበ ውሳኔ ውጤታቸውን ደምረው የጨረሱ የምርጫ ክልሎች ወደ ማዕከል አያመጡ መሆኑን አንስተው ÷እስካሁን 29 የምርጫ ክልሎች ወደ ማዕከል ገብተው የሶስት ምርጫ ክልሎች ውጤት በቦርዱ ታይቶ ይፍ ሆኗል ብለዋል።

በተጨማሪም ህዝበ ውሳኔ በተካሄደባቸው 22 የምርጫ ክልሎች ቅድመ ውጤት ይፍ የሆነ ሲሆን÷ አጠቃላይ የምርጫ ድምርን ውጤት በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች በመታገዝ በቦንጋ ማስተባበሪያ ቢሮ ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.