Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ አፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሀይል በቀጠናው ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ የቀጠናውን ሰላም ከማስጠበቅ አንፃር በምን መልኩ መስራት እንደሚገባ የተጠባባቂ ሀይሉ ስትራቴጂ ከፍተኛ አማካሪዎች ውይይት እያደረጉ ነው።

በዚህ ወቅትም ቀጠናው በተለያዩ ምክንያቶች ግጭት የሚፈጠርበት ቀጠና በመሆኑ ግጭት ከመፈጠሩ በፊት የቀጠናውን ሰላምን ለማስጠበቅ እንዲሁም ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ግጭቶችን ለማብረድ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ሁሉም አባል ሀገራት የምስራቅ አፍሪካን ሰላም እና ደህንነት ከማስጠበቅ አንፃር ዝግጁ መሆናቸውን የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሀይል ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው ሽፈራው ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ ምስራቅ አፍሪካ በብቃት የተደራጀ ሀይል ያለው እና የሰላም ቀጠና የሚል ስም እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሔድ ይሆናል።

 

በመድረኩ የቀጠናውን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲሰሩ ከአምስት የቀጠናው ሃገራት አማካሪዎች ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቅድስት ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.