Fana: At a Speed of Life!

ምሽግ ሲቆፍሩ ነበር ተብለው የተጠረጠሩት ሌተናል ኮሎኔል ኤፍሬም የህወሓት ቡድን አስገድዷቸው ምሽግ ሲቆፍሩ እንደነበር ለችሎት ገለጹ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 27፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለህወሓት ጸረ ሰላም ቡድን ምሽግ ሲቆፍሩ ነበር ተብለው የተጠረጠሩት ሌተናል ኮሎኔል ኤፍሬም አብርሃ የህወሓት ቡድን አስገድዷቸው ምሽግ ሲቆፍሩ እንደነበር ለችሎቱ ገለጹ።

ተጠርጣሪው የመከላከያ የኮንስትራከሽን ዶዘር ኦፕሬተር የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል ኤፍሬም ጨምሮ 7 መኮንኖች በቀረበበት መዝገብ ነው ይህንን ያሉት።

ተጠርጣሪዎቹ በተጠረጠሩበት ህገመንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል መናድ ሙከራ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ሰፊ የምርመራ ስራ ለችሎቱ አብራርቷል።

መርማሪ ፖሊስ ቀረኝ ላላቸው ምርመራዎች ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ጠይቋል።

1ኛ ተጠርጣሪም መርማሪ ፖሊስ አብርሃ የህወሓት ቡድን አስገድዷቸው ምሽግ ሲቆፍሩለት እንደነበር በችሎት ገልጸው ታግቼም ነበር ብለዋል።

ሌሎች ተጠርጣሪዎችም በየደረጃው ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት የለንም ሲሉ ተከራክረዋል ፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በቀረቡት ሰባቱ ተጠርጣሪዎች ላይ መዝገብ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ በይደር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል

በሌላ በኩል ሜጀር ጄኔራል ገብረ መድህን ፍቃዴ (ወዲ ነጮ) ጨምሮ ሰባት ከፍተኛ መኮንኖችም ፍርድቤት ቀርበዋል።

ፖሊስ የጠየቀባቸውን ተጨማሪ ምርመራ ምክንያት ተቃውመው ተከራክረዋል።

ችሎቱም መዝገቡን መርምሮ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ 10 ተጨማሪ ቀናትን ፈቅዷል።

እንዲሁም እያንዳንዳቸው የተጠረጠሩበትን ተሳትፎ በቀጣይ እንዲቀርብ ታዟል።

 

በታሪክ አዱኛ

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.