Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ፕሮፓጋንዳ የምዕራባውያን ሚዲያ ሴራ ነው – ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጀራልድ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባልሲሊ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤት እና የዊልፍሬድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሣይንስ የትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጀራልድ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ፕሮፓጋንዳ የምዕራባውያን ሚዲያ ሴራ መሆኑን ገለጹ።

ፕሮፌሰር አን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት አስተያየት የምዕራባውያን ሚዲያ በኢትዮጵያ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ መክፈታቸውን አንስተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም “ህወሓት ወደ አዲስ አበባ ገብቷል” እና የመሳሰሉትን የሃሰት መረጃዎች የሚነዙት የአሸባሪ ቡድኑ ደጋፊዎች እንደሆኑም ገልጸዋል።

ይሁን እንጅ ምንም ዓይነት የህወሓት ወታደር ወደ አዲስ አበባ አለመግባቱንም ያስረዳሉ።

አን ህወሓት በሰሜኑ ክፍል በአማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ እንደፈጸመ መረጃው እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ከሎስ አንጀለስ ወደ አዲስ አበባ የመጡት እና በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩት ኢትዮ – አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዳኛቸው ተሾመ በበኩላቸው ÷ አዲስ አበባ በሕወሓት ቁጥጥር ስር ልትገባ ነው የሚለው መረጃ ሠይጣናዊ ዕቅዳቸውን የሚያንጸባርቅ እና የአገርን ክብር የሚነካ ነው ሲል ይናገራሉ፡፡

አያይዘውም የውጪ ዲፕሎማቶች፣ ምግባረ ሠናይ ድርጅቶች እና ኮርፖሬሽኖች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡና በአገሪቷ ላይ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ጥፋቶች እንዲከሰቱ ለማድረግ የተሸረበ ሴራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚሳኤል ሊመታ ይችላል ተብሎ በአሜሪካ የወጣው መረጃም መሰረተ ቢስ እንደሆነና አየር መንገዱ ከውጪ በረራ የሚያገኘውን የውጪ ምንዛሬ እንዲያጣ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ይህ አገሪቷን የማሽመድመድ ሴራም በምዕራባውያንና በአሜሪካ በቅንጅት እየተሰራም ነው ማለታቸውን “የብላክ አጀንዳ ሪፖርት” ኤዲተር አን ጋሪሰን በዛሬው ዕለት በዩቲዩብ ባጠናቀረችው ዘገባዋ አመላክታለች፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.