Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም ምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ነው የሚጠበቀው።

እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ስርዓትን ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ እና የሚናማታ ስምምነትን ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎችም ይመራል።

በተጨማሪም ዓይነ ስውራን፣ ለንባብ የእይታ ችግር ላለባቸው እና በመደበኛ የንባብ ስልት ለማንበብ አካላዊ ችግር ላለባቸው ሰዎች የቀለም ጽሁፍ ህትመት ስራዎችን ተደራሽነት ለማመቻቸት የወጣውን የማራካሽ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የሚመራ ይሆናል።

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በኳታር መንግስት መካከል የተፈረመውን የኢንቨስትመንት ማስፋፋት እና ጥበቃ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም በአፍሪካ ህዝቦች እና ሰዎች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ አረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ይመራል።

በሃገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎችን ጥበቃና ድጋፍ የማድረግ የአፍሪካ ህብረት የካምፓላ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት በዛሬው መደበኛ ስብሰባ ከሚጠበቁት ውስጥ ነው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.