Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው  የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አፅድቋል፡፡

ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቡን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አቡ ብርኪ÷ ምክር ቤቱ  ረቂቅ አዋጁን ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴው በተለያዩ ጊዜያት ከአስረጂዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገበትና በቂ ግብዓትም የተገኘበት መሆኑን ለምክር ቤት አስረድተዋል፡፡

በውይይቱም የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አገልግሎት ላይ ሰፊ የህግ፣ የአሰራር፣ በአንዳንድ ጠበቆች ላይ የብቃትና የስነ-ምግባር ችግሮች እየተስተዋሉ መምጣቱን በጭብጥነት መለየታቸውን አብራርተዋል፡፡

አያይዘውም የጥብቅና ፍቃዱ ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑ አገልግሎቱ በሚጠበቅበት ደረጃ እንዳያድግና የሙያ ነጻነቱን በጠበቀ መልኩ አገልግሎቱ እንዳይሰጥ ማድረጉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የጥብቅና ህጎች ሀገሪቱ ካለችበት አጠቃላይ ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎች አንጻር ሊኖሯት የሚያስፈልጉ የጥብቅና ድርጅቶችን በተደራጀ ሁኔታ የሚመሩ ጠበቆች አለመሆናቸውን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁም አንዳንድ አንቀጾችን ሙሉ በሙሉ በሌሎች አንቀጾች ከመተካት ጀምሮ በርካታ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ነው ባቀረቡት ሪፖርት የጠቆሙት፡፡

በመጨረሻም የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳዳር ረቂቅ አዋጅ የሀገሪቱን ዜጎች ፍትህ የማግኘት እና የህግ የበላይነት በማረጋገጡ ሂደት ጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች የሚኖራቸው ድርሻ የጎላ እንዲሆን እንዲሁም የጠበቆችን ብቃትና የስነ ምግባር ችግር የሚፈታ፣ መብትና ነጻነት የሚስጠብቅ፣ የተገልጋዮችን መብት የሚስከብር በመሆኑ  ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን እንዲያፀድቀው የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳዳር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1249/2013 ዓ.ም አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ከምክር ቤቱ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.