Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባዋ በተገኙበት ሰረገላ የታክሲ አገልግሎት በይፋ ስራውን ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ሴቶች ብቻ የሚያሽከረክሩት ሰረገላ የታክሲ አገልግሎት በይፋ ስራ ጀመረ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ሰረገላ የታክሲ አገልግሎት በመዲናዋ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል ይረዳል ብለዋል፡፡

እንዲሁም የትራንስፖርት ጥራቱን  ከፍ ለማድረግ በሴት አመራር እና አሽከርካሪዎች የስራ ብቃት ብርታት፣ እውቀት፣ ችሎታ እና ጥንቃቄ

በማንኛውም የስራ መስክ በጥንቃቄ በማገልገል እና ማህበራዊ ተጸእኖ በመፍጠር ሴቶች ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ ጠቅሰዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ሰረገላ የትራንስፖርት ድርጅት ይህንን አራዓያነት ያለውን ንግድ በከመዲናዋ በመጀመሩ የእንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.