Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ እና ሌሎች ኃላፊዎች ከመምህራን ጋር ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ መምህራን ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ከመምህራን ጋር በተደረገው ውይይት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በሁሉም አቅጣጫዎች  ከለውጡ መነሻ አንስቶ እዚህ እንዲደርስ ካደረጉት አካላት አንዱ አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የጀመረችው ለውጥ ትኩረት የሀገረ መንግስት ግንባታ ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች ይችን ሀገር ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር ሁሉም የራሱን አሻራ ሊያሳርፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የትምህርት ሚንስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ በተገኘው ለውጥ ሁሉንም እኩል ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ በቅድሚያ ሀገርንና ትውልድን በጥሩ ስነምግባር መገንባት ያስፈልጋል።

ለነዚህም መምህራን እና የዘርፉ አካላት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

አያይዘውም ያልተሟሉ የትምህርት ግብዓቶችን እናሟላለን ብለዋል።

ከመምህራን ያነሱትን የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች የጥቅማጥቅም ጥያቄዎችን በተመለከተ የከተማ አስተዳደሩ የሚችለው እያደረገ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ አዳነች በቅርቡ ለመምህራን የተደረገውን የ3ሺህ ብር የቤት አበል ጭማሪን ለአብነት አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው ሀገራዊ ለውጡ ግቡን አንዲመታ እና ሀገራዊ  አንድነት እና መግባባት እንዲፈጠር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት አለበት ብለዋል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ባለፉት አንድ ወራት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ሰፊ ውይይት መካሄዱን አቶ መለሰ ተናግረዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ 3 ሺህ በላይ ርዕሳነ መምህራን፣መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የትምህርት ዘርፍ አመራሮች ተሳተፈዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከተማሪ ወላጅ ኮሚቴ እና ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በተጨማሪም በውይይቱ የተሳተፉ ርዕሳነ መምህራን፣መምህራን  እና ሱፐርቫይዘሮች የአንድነትና የወዳጅነት ፓርክን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.