Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ምክት ከንቲባዋ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት÷በከተማችን እና በዙሪያዋ የምትገኙ ነዋሪዎች ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ  ብለዋል።

ዘንድሮ  ከምንጊዜውም በተለየ መልኩ 125ኛዉን የአድዋ የድል በዓል በአዲስ አበባ  በድምቀት አክብረናልም ነው ያሉት ።

በልዩ ድምቀት በተከበረው በዚህ 125ኛው የአድዋ ድል በዓል ላይ ከዋዜማው አንስቶ በሰላም እና በድምቀት እንዲከበር ላደረጋችሁ እና ላስተባበራችሁ ወጣቶች ፣ የፖሊስና የፀጥታ አካላት :በከተማችን እና በዙሪያዋ የምትገኙ ነዋሪዎች  እንዲሁም አመራሮች ከፍ ያለ ምስጋናዬን በከተማ አስተዳደሩና በእራሴ ስም ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

አያይዘውም ተያይዘን፣ ተደጋግፈን እና በአብሮነት የስንሰራ  ዘላቂ  ሰላማዊ ግኑኘነት እያንዳንዳችንን ተጠቃሚ  የሚያደርግ ነውና በምንችለው ሁሉ በመደጋፍ  ህዝባዊ አንድነታችንን አጠናክረን እንቀጥል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.