Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የትግራይ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የትግራይ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱ በሃገሪቱ ባለው አሁናዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡
በውይይቱ ላይ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ አንስተዋል፡፡
ችግሩ እዚህ ደረጃ እንዳይደርስ የፌደራል መንግስቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ የሄደባቸውን ርቀቶችም ተጠቅሰዋል፡፡
በዋናነትም ፅንፈኛው ቡድን ህዝቡን ሽፋን በማድረግ የራሱን ጥቅም ሲያሳድድ መኖሩን እና ጥፋቶችን ሲያቀነባብር መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
የነበረውን ሂደትም መንግስት በታላቅ ትዕግስት እና አስተዋይነት ሲመለከትና የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም ነው ያነሱት፡፡
ምክትል ከንቲባዋ በከተማዋ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጆች እና ባለሃብቶች ለሰላምና ለአንድነት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታወች ላይም መክረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለስ ዓለም ተገኝተዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.