Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጫን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጫን ጎብኝተዋል፡፡

የሀይል ማመንጫው አልፎ አልፎ የሚያጋጥመውን የግብዓት አቅርቦት እና የበጀት ችግር መቅረፍ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ከስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጫ በ32 ሄክታር መሬት ላይ በአመት 185 ጌጋ ዋት ሀወር የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጭ ሲሆን አሁን ላይ የገቢ አቅሙ ገና በመሆኑ ምክንያት የግብዓትና የበጀት ችግር እንደገጠመው የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ብሩክ ኤባ ገልፀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ምክትል ከንቲባዋ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታን የጎበኙ ሲሆን በውስጡ ያሉ ሰራተኞችን በገጠማቸው ችግሮች ዙሪያ አነጋግረዋቸዋል፡፡

በዚህም የተለያዩ መሟላት የሚገባቸውን የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን ቦታው ከመጥበቡ የተነሳ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ እየፈጠረ ስላለው ጫና ዶክተር እሸቱ ለማ የደረቅ ቆሻሻ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አብራርተዋል።

በጉብኝታቸው ማጠቃለያ ምክትል ከንቲባዋ በተቋሙና አካባባው ላይ ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ላሉ አካላት ያላቸውን ክብር በመግለፅ አስተዳደሩ በተነሱት ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ ለማምጣት አብሯቸው እንደሚሰራ መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.