Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ከጽዳት ባለሙያዎችና ከጃንሜዳ አካባቢ ማህበረሰብ ጋር የፅዳት ስራ አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከጽዳት ባለሙያዎችና ከጃንሜዳ አካባቢ ማህበረሰብ ጋር በመሆን አካባቢውን የማፅዳት ስራ አከናውነዋል።
በጃንሜዳ ውስጥ ያሉ አትክልት ነጋዴዎች ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ተዘጋጀላቸው የአትክልት መሸጫ ስፍራዎች እንደሚዘዋወሩ ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል ።
ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል ዝግጁ ለማድረግ እና ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ በተከታታይ የማጽዳት ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል ።
ሸማቹን እና አምራቹን አንድ ላይ ማገናኘት የሚያስችሉ የአትክልት እና መሰል መገበያያ ስፍራዎች በየክፍለ ከተማው ተደራሽ የማድረግ ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ወ/ሮ አዳነች ጠቁመዋል፡፡
ነጋዴውም ሆነ ነዋሪው ህብረተሰብ ጃንሜዳን ወደ ቀድሞው አገልግሎቱ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከተማው ፕሬስ ሰክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.