Fana: At a Speed of Life!

ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ሙግት መድረክ በአማራ ክልል ደረጃ በባህር ዳር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብልጽግና ወጣቶች ሊግ አዘጋጅነት በሀገር አቀፍ ደረጃ በከተሞች እየተካሄደ ያለው አንደኛው ዙር ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ሙግት መድረክ ዛሬ በአማራ ክልል ደረጃ በባህር ዳር ተጀመረ።

በመድረኩ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ምሁራን ወጣቶች እየተሳተፋበት ሲሆን የሀገረ መንግስት ግንባታና የወጣቱ ሚና በሚል ርዕስ የተሰናዳ ነው።

የሀገረ መንግስት ግንባታ ምንነት፣የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደትና ት/ት የሚወሰድባቸው ጉዳዮች፣የሌሎች ሀገራት የሀገረ መንግስት ግንባታ ልምዶች፣ለውጡና የሀገረ መንግስት ግንባታ እርምጃዎች እንዲሁም የተጠናከረ የሀገረ መንግስት እውን ማድረግ ይቻል ዘንድ የወጣቱ ሚና የሚሉ ነጥቦች ተዳሰውበታል።

ብዝሀነታችንን ጠብቀን አንድነታችንን የምናጠናክርባት፣ሰላምና ብልጽግና የተረጋገጠባት፣ዜጎች በእኩልነት ተንቀሳቅሰውና ሰርተው ህይወታቸውን የሚመሩባትን ኢትዮጵያ ማጠናከር ይቻል ዘንድ ሀገረ መንግስቱ ሊቆምባቸው የሚገባው ምሰሶና የወጣቱ ሚናም በሰፊው እየተመከረበት ነው።

በመድረኩ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኋላፊ የተከበሩ አቶ አብርሀም አለህኝ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.