Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ ከፈለጉ አሸባሪው ህወሓት ላይ እርምጃ መውሰድ አለባቸው- ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጌራልድ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ ጽኑ ፍላጎት ካላቸው አሸባሪው ሕወሓት ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው በካናዳ ዊልፍሪድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር አን ፊትዝ -ጌራልድ ገለጹ።

አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት በሕዝብ የተመረጠ መንግስትንና አሸባሪው ህወሓትን በእኩል ሚዛን ማስቀመጣቸው ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑን ነው ፕሮፌሰሯ የተናገሩት።

ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ ጽኑ ፍላጎት ካላቸው አሸባሪው ሕወሓት ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

ፕሮፌሰር አን ፊትዝ-ጌራልድ ለኢዜአ እንደገለጹት ÷ በሰሜን ዕዝ ላይ አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸም ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት የጸጥታ ችግር መንስኤ የሆነው አሸባሪው ህወሓት በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የክህደት ጥቃት የፈጸመ ቡድን ነው።

በመሆኑም ይህ ቡድን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመረጠ መንግስት ጋር የሞራል እኩልነት መስጠት መሰረታዊ ስህተት መሆኑን አስገንዝበዋል።

“በዚህም አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት ውግንና ያለውና ሚዛናዊ እይታ የጎደለው አካሄድ እየተከተሉ ነው” ብለዋል።

ይህ የተሳሳተ አካሄድ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት እንደማያግዝም አመልክተዋል።

“በኢትዮጵያ አሁን ስልጣን ያለው መንግስት ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ያለው ነው፤ ድምጽ ለመስጠት የወጣው ሕዝብ ቁጥር በቅርብ ጊዜ ዓለማችን ላይ ከተደረጉ ምርጫዎች የሚበልጥ ነው” ብለዋል ፕሮፌሰሯ።

ለግጭቱ መከሰት፣ መራዘምና መስፋፋት እንዲሁም ለዜጎች መከራና ስቃይ ተጠያቂ በሆነው አሸባሪው ህወሓት ላይ ምዕራባውያኑ እርምጃ አለመውሰዳቸው የተሳሳተ መንገድ እየተከተሉ እንደሆነ ማሳየቱን ገልጸው ÷ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና ማሳደራቸው ተገቢነት እንደሌለው ገልጸዋል።

ምዕራባውያኑ አሸባሪው ህወሓት የፈጸማቸው ድርጊቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ አለመውሰዳቸው አስገራሚ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህ አካሄድ የባይደን አስተዳደርን ጨምሮ የምዕራባውያን አገራትን ለጦርነቱ መራዘመና እየደረሰ ላለው አስከፊ ሰብዓዊ ጉዳት ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑን ነው ፕሮፌሰር አን የገለጹት።

በመሆኑም ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ አሸባሪው ህወሓት ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድና ተጠያቂ ማድረግ እንዳላበቸው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ እየተከተሉት ያለውን ፖሊሲ ዳግም በማጤን ገንቢ ሚና መጫወት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.