Fana: At a Speed of Life!

ም/ርዕሰ መሥተዳድር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ በውኃ የተጥለቀለቁ አካባቢዎችን ሁኔታ ተመለከቱ

አዲስ አበባ፡ መስከረም 6 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በጣና ሐይቅ ሞልቶ መፍሰስ ምክንያት በውኃ የተከበቡና የተጥለቀለቁ የፎገራ ወረዳ አካባቢዎችን ሁኔታ በአካል ተገኝተው ተመልክተዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ዋገጠራ፣ ስንደዬ፣ አባጋሹ፣ ባርጌና ሴላድባ፣ ማርያም ምድር እና አጎራባች አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቀያቸውና የእርሻ ማሳቸው በውኃ ተከቧል ።

አርሶ አደሮችም የውኃው መጠን በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ቀያቸውን በመልቀቅ እየሸሹ ሲሆን እንስሳትም አደጋ ውስጥ መውደቃቸው ነው የተመላከተው።

ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ እያደረጉት ያለው ምልከታ የክልሉ መንግሥት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን አብመድ ዘግቧል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.