Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትሜንት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትሜንት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ጋር በስልክ ተወያዩ።

አቶ ደመቀ በሰሜን የአገራችን ክፍል ስለተካሄው የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ በትግራይ ክልል ሰብአዊ ዕርዳትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተካሄደ ያለውን ተግባር፣ የህወሃት ጁንታ ያፈረሳቸውን መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመጠገን ወደ ተግባር ለማስገባት እየተካሄደ ያለው ጥረትና በጥረቱ የተገኙ ውጤቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኤርትራ ስደተኞች አያያዝ፣ በማይካድራና ሌሎች አካባቢዎች የተፈፀሙ ኢሰብአዊ ድርጊቶችና ድርጊቶቹን ለማጣራት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በተመለከተም ለረዳት ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንዲሁም በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲፈጠር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችንም በዝርዝር አስረድተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር በትብብር ለመሥራት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ገልፀዋል።

ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ስኬት የአሜሪካ ስኬት መሆኑን ገልፀው፣ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መጠናከር ያላቸውን በጎ ስሜት ገልፀዋል።

ኢትዮጰያ ያጋጠማትን ችግር ለመቋቋም እያደረገች ያለውን ጥረትና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላደረጉላቸው ገለፃ ማመስገናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.