Fana: At a Speed of Life!

ሞሪንጋ ተክል ለመድሀኒትነት እንደሚውል በምርምር ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ሞሪንጋ (ሽፈራው) እየተባለ የሚጠራው ተክል ለተለያዩ በሽታዎች ለመድሃኒትነት መዋል እንደሚችል በምርምር መረጋገጡን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
በሞሪንጋ ዙሪያ በተደረጉ የምርምር ስራዎች ዙሪያ የሚመክር መድረክ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ የኢኒስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ እንደገለጹት ኢኒስቲትዩቱ የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት ለማሟላት በአዲስ መልክ ተደራጅቶ የአስር አመት መሪ ዕቅድ በማውጣት ወደ ስራ ገብቷል።
“ሀገር በቀል ዕውቀት በመጠቀም ባህላዊ መድሀኒቶችን በዘመናዊና ሳይንሳዊ ጥናቶች ለመደገፍ የትኩረት አቅጣጫ በማደረግ ከሀገር ውስጥና አለም ዓቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርጋቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች ጉልህ ስፍራ አላቸው” ብለዋል።
ኢኒስቲቲውቱ ካተኮረባቸው መካከል ሞሪንጋ ለህብረተሰቡ ደህንነት ደረጃውን የጠበቀ ጥቅም እንዲሰጥ ማድረግ አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል ።
እጽዋቱ ለመድሀኒትነት ያለውን ፋይዳ በምርምርና ጥናት በመለየትም በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሰራ እንደሚገኝ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.