Fana: At a Speed of Life!

ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ በፍጥነት እንቅልፍ  ለመተኛት ጥሩ አማራጭ ነው -ጥናት

አዲስ አበባ፣ጥር 5፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ በፍጥነት እንቅልፍ  ለመተኛት ጥሩ አማራጭ  መሆኑን ጥናት አመለከተ፡፡

ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ በፍጥነት እንቅልፍ  ለመተኛት  ከማገዙም በተጨማሪ  ብዙ ጥቅሞች ማስገኘቱን ጥናት አመላክቷል፡፡

በዚህ ጥናት መሠረት 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ለመታጠብ ገንዳን እንደሚመርጡ ተጠቁሟል፡፡

ጥናቱ በሙቅ  ውሃ መታጠብ ለጥሩ እንቅልፍ፣ለመዝናናት እና ህመምን ለማስታገስ የተሻለ ምርጫ  መሆኑን ነው ያመለከተው፡፡

ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት በህይወት  የበለጠ ምርታማና ውጤታማ መሆኑን እንደሚያስችል እና ይህም ነገሮችን በፍጥነት መሳካት እንዲኩ ያስችላል ተብሏል፡፡

በምሽት ሞቅ ባለ ውሃ ሰውነትን መታጠብ  ሰውነት ሜላቶኒን የተባለ ሆርሞን በመልቀቅ በፍጥነት እንቅልፍ እንዲወስዶት ያደርጋል ተብሏል፡፡

የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ወደ መኝታ ከመሄድ ከ 1 እስከ 2 ሰዓታት በፊት ሰውነትን በሙቅ ውሃ መታጠብ በጥናቱ ተመክሯል፡፡

በተጨማሪም በጭንቀት  እና በእንቅልፍ እጦት የሚሰቃዩ ሰዎች  በሙቅ ውሃ  ቢታጠቡ  ጡንቻዎች እንዲረጋጉ እና ዘና እንዲል ያደርጋል  ነው የተባለው፡፡

በእንቅልፍ  ወቅት በጉልበት እና በመገጣጠሚያ ህመም የሚረበሹ ከሆነ ፣በመገጣጠሚያዎች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ እና ጡንቻዎችዎን ዘና ለማድረግ  ሙቅ ውሃ  መድሀኒት ነው ተብሏል፡፡

በበሌላም በኩል ከሙቅ ውሃ በተጨማሪ የቀን ጭንቀቶትን  ለማስወገድ በመታጠቢያው ውሃ ውስጥ አስፈላጊ ዘይቶችን በመጨመር እና ሙዚቃን በማዳመጥ ዘና በማለት ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት እንደሚቻልም ጥናቱ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡-https://www.psychologytoday.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.