Fana: At a Speed of Life!

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለኪልባቲ ረሱ ዞን ነዋሪዎች 7 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የእህል ወፍጮዎችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠመራ ዩኒቨርሲቲ በአፋር ክልል በአሸባሪው ህውሓት ወረራ ተፈናቅለው ለነበሩ የኪልባቲ ረሱ ዞን ነዋሪዎች ማቋቋሚያ 7ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገዙ የእህል ወፍጮዎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አሕመድ ያሲን÷ የተደረገው ድጋፍ በጦርነቱ ለተጎዱ በኪልባቲ ረሱ ዞን ውስጥ ለሚገኙ ሰባት ወረዳዎች አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ከወፍጮዎቹ የሚገኘው ገቢም÷ቤተሰቦቻቸው በጦርነቱ መስዋዕት የሆኑባቸው ወገኖች እንዲቋቋሙበት ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል፡፡
 
የኪልባቲ ረሱ ዞን አስተዳደር አቶ መሀመድ እንድሪስ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከጦርነቱ በፊት በምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ከዞኑ ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ገልጸው÷ በጦርነቱ ወቅትም ለማህበረሰቡ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ከጎናችን ነበር ብለዋል፡፡
 
አሁን ላይ ደግሞ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁመው÷ ለዚህም ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
 
ድጋፉ በቀጣይ የማህበረሰቡን ኑሮ ሊያሻሽሉ በሚችሉ ሥራዎች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዩኒቨርሲቲው መረጃ አመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.