Fana: At a Speed of Life!

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የአፋርኛ ቋንቋን በሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋርኛ ቋንቋ ሳይንሳዊ ጥናቶች እና ምርምሮች የሚካሄዱበት እንዲሆን ለማድረግ እና ወደ ሁለተኛ ድግሪ ለማሳደግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቅቀው ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆለታል ሲል የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡
በዚህ መሠረት አፋርኛ ቋንቋን ወደ ሁለተኛ ዲግሪ ለማሳደግ የተደረገው ዝግጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ይቀርባል ተብሏል፡፡
የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶክተር መሀመድ ኡስማን ዳራሳ እንዳሉት÷ አፋርኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በጅቡቲ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተናጋሪ ያለውና ድንበር ተሻጋሪ ቋንቋ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲያው በቀጣይ የአፋርኛ ትምህርት ወደ ሦስተኛ ዲግሪም ከፍ ለማድረግ ይሠራል ማለታቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.