Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያን ለመነጠል እየሞከሩ ያሉ ሃገራት እራሳቸውን እያዳከሙ ነው – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያን ለመነጠል እየሞከሩ ያሉ ሃገራት የራሳቸውን ኢኮኖሚ እያዳከሙ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ።
 
ፑቲን በእስያ አውሮፓ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሩሲያን ማግለልና መነጠል የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።
 
አያይዘውም ይህን ለማድረግ የሚሞክሩና በሩሲያ ላይ የሚያሴሩ ሃገራት እራሳቸውን ይጎዳሉም ነው ያሉት።
 
“ዓለም ላይ ጠንካራ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት አሁን ላይ ከባድ የዋጋ ግሽበትና ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥ ዜጎች ቁጥር እያስተናገዱ” መሆኑንም አመላክተዋል።
 
ከዚህ ጋር ተያይዞም ዓለም አቀፉ ቀውስ እጅግ ተባብሷል ማለታቸውን ሺንዋ በዘገባው አመላክቷል።
 
“ይህም መላው የኢኮኖሚ ስርአትና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ጉዳይ” መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
 
ሃገራትን ለማዳከም በማሰብ የሚጣሉ ማዕቀቦችና ገደቦችም እርባና ቢስና ጠቀሜታ የሌላቸው ናቸው ብለዋል ፑቲን በንግግራቸው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.