Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለአሜሪካ ተጽዕኖም ሆነ ማባበያ እጅ አንሰጥም አለች

አዲስ አበባ ፣ጥር 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለአሜሪካ ተጽዕኖ ወይም ማባበያ እጅ አትሰጥም ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ርያብኮቭ ተናገሩ።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለስፑትኒክ የዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ÷በጥር ወር በሁለቱ ሀገራት በጄኔቫ ከተዘጋጀው የስትራቴጂያዊ የሰላም ድርድር በኋላ ሩሲያ ለአሜሪካ ግፊት ወይም ማባበያ እጅ አትሰጥም ፤ አገራችን በተፅዕኖ ውስጥ ሆና ምንም ዓይነት ስምምነት አታደርግም።
ቀጣይነት ባለው የሁለቱ ሀገራት ድርድር ከምዕራቡ ዓለም በሚመጣው የማያቋርጥ ጫና እና ዛቻ ተገፍተን ስምምነት አናደርግም ያሉት ሰርጌይ ርያብኮቭ፣ በጫና ምክንያት ሊደረጉ የሚችሉ ስምምነቶች የሩሲያን ደህንነት ፍላጎት ስጋት ውስጥ የሚከቱ ናቸው፣ ስለሆነም በምዕራባውያኑ ጫና የሚመጣ ስምምነትን አንቀበልም ሲሉ አስገንዝበዋል።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም በጄኔቫ በሚካሄደው ውይይት የሞስኮ አቋም፥ የኔቶ መስፋፋት እንዲቆም እና በሩሲያ ድንበሮች አካባቢ የጥቃት የጦር መሳሪያዎች እንዳይገቡ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሁን እንጅ ዩናይትድ ስቴትስ ሞስኮ የአንድ ወገን ስምምነት እንድታደርግ ጫና ማድረጓን ከቀጠለች ሩሲያ በመጪው ውይይቶች ላይ ከባድ ፈተና እንደሚጠብቃት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች እንደሚናገሩ ነው የቲ አር ቲ ዘገባ የሚጠቁመው።
የፀጥታ ጉዳይን አስመልከቶ የሚደረገው የኔቶ-ሩሲያ ምክር ቤት ስብሰባ ጥር 12 በብራስልስ እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ሲሆን፥ በጥር 13 ደግሞ በቪየና በአውሮፓ የደህንነትና ትብብር ድርጅት (OSCE) የውስጥ ምክክር ይደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.